Thursday, July 30, 2015

ጎዞ ከህፃናት ጋር




ጎዞ ከህፃናት ጋር
በአለም አቀፍ በረራ እድሚያቸው ከሁለት አመት በታች የሆኑ ህፃናት ይከፍላሉ። ግን አንዳንድ ተሳፋሪዎች በሃገር ውስጥ በረራ ለምደው ስለ ልጆች በረራ ትከፍላላችሁ ሶባሉ ትንሽ ቅር ይላቸዋል። ህጉ ከአየር መንገዶች ጋር ባለው ውል የሚሰራ ሲሆን በ አብዛኛው ግን አንድ አይነት ነው። የዚህ ፅሁፍ አንባቢ ይሆናሉ ብለን ካስብናቸው ውስጥ በአብዛኛው ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ መንገድኞችን ስለሆነ ከዘጣና እጅ  (90%) በላይ የሚሆነው ደግሞ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ይዞ  የሚሄድ ስለሆነ እስኪ ካለን ልምድ እናካፍላች ሁ።

ከሁለት አመት በታች ልጅ ይዘው ሲጓዙ ለልጅዎ ከዋናው መደበኛ ክፍያ አስር በመቶ (10%) ይከፍላሉ። ህፃኑ የራሱ የሆነ መቀምጫ አይሰጠውም። እርሰዎ ታቅፈውት  መሄድ ሲኖርብወት ለህፃኑ/ኗ የራሱ/ሷ የሆነ ሻንጣ አይፈቀድለትም/ላትም:: ነገር ግን አንዳንዴ የ አየር መንገዱ ሰራትኞች በማዝንም ይሁን ለመርዳት ብለው ለህፃኑ አስፍላጊ የሆኑ ነገሮችን በነፃ ሊጭኑ ይችላሉ። ያ ማለት ሁሌም እሺ ይላሉ ስላልሆነ አንዳንዴ  ይክፈሉ ቢባሉ መለመን እንጂ መከራከሩ አያዋጣም ። እንዲሁም እድሚያቸው በጣም ለጋ (ኒው ቦርን) በወራት ለሚጠጉ ልጆች የተወሰኑ ቤዝኔት የሚባሉ የህፃናት መተኛውች አሉ፣ እነዚህ መተኛውች የተወስነ ቁጥር ስላላቸው አየር መንገዱ ለእርስዎ ልጅ ሊኖረውም ሆነ ላይኖረው ይችላል። ነገር ግን ለምን የለም ወይም አልተሰጠኝም ብሎ አምባ ጓሮ መፍጠር አያስፈልግም። ሁሌም በጉዞ ላይ ጥሩ ጠባይ ያለው ሰው እሱም እራሱን ሳያመው ለሌላው መንገደኛም የራስ ምታት ሳይሆን በሰላም ይደርሳል።

ታዲያ ልጅዎ ከሁለት አመት በታች ከሆነው/ ከሆናት ቶሎ መጓዙ ወጪወትን ይቀንሰዋል። ለምሳሌ ልጆች ሁለት አመት ካለፋቸው እስከ አስራ ሁለት አመታቸው ድረስ የበርራውን አዋዊዎች ከሚከፍሉት ሰባ አምስት እጅ (75%) ይከፍላሉ ማለት ነው። ያም ብዙ ወጪ ነው።
በበለጣ ለመረዳት እባክዎ በስልክ ቁጥር   619 255 5530 ይደውሉልን ለመርዳት ዝግጁ ነን::

የቦ የጉዞ ወኪል