ጠቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች



ቅልለው ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቀረጥና ታክስ ከፍለው እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች
  • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈለጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡
  • አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርቦታል
  • በአምስት አመት ውስጥ ከአንድ ግዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም
  • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች እባክዎ መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡
የፖስታ አላላክ መመሪያ
  • በፖስታ ቤት አማካኝነት አገልግሎቱን የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL መሆን ይገባዋል፡፡
  • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ እባክዎት ፖስታውን  ኤምባሲ መድረሱን ለማወቅ አይደውሉ፡፡
  • ማመልከቻዎ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ውይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!
አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ
1
አመስት አመትና ከዚያ ላይ በውጭ አገር መቆየትዎን የሚያሳይ ማስረጃ አንድ ኮፒ ማቅረብ (የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ወይም ሌላ ማስረጃ)
2
ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ ፓስፖርት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በሶስት ኮፒ
3
ግሪን ካርድ በሶስት ኮፒ (የአሜሪካ ዜጋ ላልሆኑ)
4
የአገልግሎት ክፍያ $58.80 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
  • መኒ ኦርደር /Money Order/ ወይም
  • ካሽየር ቼክ /Cashier Check/ ወይም
  • ሰርቲፋይድ ባንክ ቼክ /Certified Bank Check/
5
መጠየቂያ ቅጽ  አንድ ኮፒ መሙላት (click here to download FORM)
6
የሚያስገቡት እቃዎች ዝርዝር በሶስት ኮፒ (click here to download the ITEMS)
7
ማመልከቻዎ በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ

No comments:

Post a Comment