የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ
አገልግሎት
|
እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው
ይላኩ፡፡
-
ከዚህ ቀደም የተዘጋጀ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለመረከብ ወደ ኤምባሲ በአካል መቅረብ የሚጠይቀውን
አሰራር በተገልጋዩ ህብረተሰብ ላይ መጉላላትን ፈጥሮ ስለነበር መንግስት መመሪያውን በማሻሻል ከአሁን በኋላ
የተዘጋጀልዎትን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በፖስታ ቤት በኩል እንዲደርስዎ ተደርጓል።
-
አገልግሎቱን ለማግኘት ሲያመለክቱም ሆነ ሲረከቡ በአካል ወደ ኤምባሲ መቅረብ የለብዎትም። በመሆኑም በፖስታ
ቤት በኩል ብቻ ተረክበን የምናስተናግድዎ በመሆኑ ወደ ኤምባሲው ሲልኩም ሆነ የተዘጋጀልዎትን የትውልድ
ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወደ እርሶ መልሰን ለመላክ Tracking Number ባለው FEDEX,
UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ይጠቀሙ። ኤምባሲው መታወቂያ ካርድዎ ከኢትዮጵያ
እንደተረከበ በተቻለ ፍጥነት ይልክልዎታል።
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡
መታወቂያ ካርዱን
በጊዜው ካላሳደሱ መቀጫ ስላለው እባክዎ የአገልግሎት ዘመኑ ሳያበቃ መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ፡፡
-
የአገልግሎት ዘመኑ እስካላበቃ ድረስ መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት
ይችላሉ፡፡
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም አዲሱን
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡
-
እባክዎ ከጉዞዎ ወይም ከታደሰ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ
ቢያንስ ከ45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡
|
የፖስታ አላላክ መመሪያ
-
አገልግሎቱን ለማግኘት ሲያመለክቱም ሆነ ሲረከቡ በአካል ወደ ኤምባሲ መቅረብ የለብዎትም። በመሆኑም በፖስታ ቤት
በኩል ብቻ ተረክበን የምናስተናግድዎ በመሆኑ ወደ ኤምባሲው ሲልኩም ሆነ የተዘጋጀልዎትን የትውልድ ኢትዮጵያዊ
መታወቂያ ካርድ ወደ እርሶ መልሰን ለመላክ Tracking Number ባለው FEDEX,
UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL ይጠቀሙ። ኤምባሲው መታወቂያ ካርድዎ ከኢትዮጵያ እንደተረከበ
በተቻለ ፍጥነት ይልክልዎታል።
-
የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ ወደ እርሶ ለመመለሱ ባለዎት Tracking Number በመጠቀም
ማወቅ ስለሚችሉ ወደ ኤምባሲ መደወል አይጠበቅብዎትም።
|
የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ
|
|
-
-
የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት
(አገልግሎቱ ቢያንስ ለ 6 ወራት የፀና ፓስፖርት) በሁለት ኮፒ
-
በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ማስረጃ
-
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ
ማንዋል (ሰማያዊ) ከሆነ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ
የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ
እንዲሁም አግባብ ካለው አካል የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር
ወረቀት በሁለት ኮፒ ማያያዝ፤ ወይም
-
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ
አዲሱ ማሽን ሪዴብል (ቀይ ቡኒ) ከሆነ መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ
የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ፤ወይም
-
አግባብ ካለው አካል
የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ
የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ
በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጲያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው
ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ
የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነትን ይዞ የነበረ መሆኑን
የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
-
የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው
ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና
ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click
here to download Fingerprint Capture FORM)
-
ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት
ፎቶ ግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
-
የአገልግሎት ክፍያ
200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
መኒ ኦርደር /Money Order/
-
አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS,
ወይም USPS EXPRESS MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
|
ለ. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር
ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ
ሲጠይቁ |
-
-
የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6 ወር የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት
በሁለት ኮፒ
-
ከተሰጠበት
ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት
በሁለት ኮፒ
(ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት አመት የፀና መሆን ይኖርበታል)
-
-
የባል/የሚስት
አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ
በሁለት ኮፒ
-
የኢትዮጵያ
ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ ሶስት (3) የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና
ከጀርባው ስም የተጻፈበት)
-
የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ የጣት አሻራ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ
ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም
ድርጅቶቹ የጣት አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም
ይችላሉ። (click
here to download Fingerprint Capture FORM)
-
የአገልግሎት ክፍያ
200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
መኒ ኦርደር /Money Order/
-
አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS
MAIL ) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
|
|
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡
የአገልግሎት ዘመኑ ሳያበቃ እባክዎ በጊዜው መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ፡፡
ካርዱን በወቅቱ ካላሳደሱ ከታህሳስ 01 ቀን 2007 ዓ.ም (December 10 / 2014) ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው
አዲስ የክፍያ ተመን መሰረት መቀጫ ገንዘብ ያስከፍልዎታል፡፡ ስለሆነም
ከታህሳስ 01
ቀን 2007 ዓ.ም (December 10 / 2014) ጀምሮ የመጀመሪያዎቹ 15 ቀናት በየቀኑ 3 ዶላር ሆኖ ከ16ኛው
ቀን ጀምሮ ያሉት ቀናት ደግሞ በየቀኑ 5 ዶላር ያስከፍልዎታል፡፡
-
የትውልድ
ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከ 6 ወር በላይ ሳያሳድሱ ከቆዩ ያላሳደሱበትን ምክንያትን የሚገልፅ ማመልከቻ አያይዘው
ማቅረብ ይኖርብዎታል፡፡
-
የአገልግሎት ዘመኑ እስካላበቃ ድረስ መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት
ይችላሉ፡፡
-
እባክዎ ከጉዞዎ ወይም ከታደሰ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ
ቢያንስ ከ45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡
-
-
አገልግሎት
ዘመኑ ያበቃው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና
በሁለት ኮፒ
-
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ
ካርድዎ ማንዋል (ቢጫው) ከሆነ
-
አግባብ ካለው አካል
የተሰጠና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የልደት ምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣ ወይም
-
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፓስፖርትዎ
መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ
የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ ኢትዮጵያውያን ከሆኑ/ ከነበሩ
የስጋ (Biological) ወላጆች የተገኘ የወራሽነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ በኢትዮጵያውያን ወላጆቹ
በጉዲፈቻነት የተሰጠ ኢትዮጲያዊ እንደነበረ የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሰው
ወይም የሰነድ ምስክርነት ማስረጃ በሁለት ኮፒ ፣ ወይም
-
ስልጣን ባለው የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተሰጠና
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነቱን በተጨባጭ
የሚያረጋግጥ አባቱ ወይም እናቱ ወይም ቅድመ አያቱ ቢያንስ በአንዱ የኢትዮጵያ ዜግነትን ይዞ የነበረ መሆኑን
የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በሁለት ኮፒ
-
አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6 ወር የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት
በሁለት ኮፒ
-
ሶስት (3)
የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም
የተጻፈበት)
-
በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ
በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ
(Click here to download the form) ተያይዞ ሲቀርብ እንዲሁም
አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ ተያይዞ መቅረብ
ይኖርበታል፡፡
-
የጣት አሻራ
በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ
በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት
አሻር መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
መውሰጃ
ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click
here to download Fingerprint Capture FORM)
ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን
ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅቦትም፡፡
-
የአገልግሎት
ክፍያ 200 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር /Money Order/ወይም
-
አድራሻዎ
የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL )
ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
|
|
-
-
መታወቂያው
ስለመጥፋቱ በግለሰቡ የተፃፈ ማመልከቻ
-
የታደሰ የውጭ
አገር ፓስፖርት በሁለት ኮፒ
-
የቀድሞ
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ (የመታወቂያው ኮፒ ከሌለዎት መቼ እና ከየት እንደወሰዱት የሚገልፅ
ማስታወሻ አያይዘው ይላኩ)
-
የጠፋው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ
ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ
(Click here to download the form) በሁለት
ቅጅ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር ተያይዞ መቅረብ
ይኖርበታል፡፡
-
የጣት አሻራ
በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ
በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ /Form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት
አሻር
መውሰጃ
ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (click
here to download Fingerprint Capture FORM)
ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን
ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅቦትም፡፡
-
ሶስት (3)
የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶ ግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም
የተጻፈበት)
-
የአገልግሎት
ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ
መኒ ኦርደር /Money Order/ ሆኖ
-
በጠፋ ምትክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጥ 240 ዶላር፤
-
በጠፋ ምትክ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰጥ 300 ዶላር፤
-
በጠፋ ምትክ ለሶሰተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ
ሲሰጥ
400 ዶላር፤
-
አድራሻዎ
የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው (FEDEX, UPS, ወይም USPS EXPRESS MAIL )
ከነቴምብሩ አብሮ መላክ
|
No comments:
Post a Comment